Wednesday, July 23, 2014

ምቀኝነት ለምኔ?!
ከእኛ ስኬታማነት ይልቅ የሌሎች ወድቀት ደስ የሚያሰኘን ከሆነ፣ ከኛ ማግኘት ይልቅ የሌሎች ማጣት ደስ የሚያሰኘን ከሆነ፣እኛ የምንሰራው ስራ እኛን ለማስደሰት ሳይሆን ሌሎችን ለማስከፋት ከሆነ፣ በእኛ ጋብቻ ከመደሰት ይልቅ የቀድሞ ፍቅረኛችን በእኛ ጋብቻ ሲያዝኑ የሚያስደስተን ከሆነ፣ የእኛ በከፍተኛ ውጤት መመረቅ ሳያስደስተን በሌሎች ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ደስ የምንሰኝ ከሆነ፣ ከእኛ ሹመት ይልቅ የሌላው ሽረት የሚያስደስተን ከሆነ፣ከእኛ ጤንነት ይልቅ የሌሎች ህመም ካስደሰተን፣ በእኛ በህይወት መኖር ፈጣሪን ማመስገን ሲገባን በሌላው ሰው ሞት ፈጣሪን ካመሰገንን ታድያ የእኛ ደስታ ሰዎች ሲቸገሩና ሲጎዱ ከሆነ ማነው ከእኛ ጋር ወዳጅ የሚሆነው? ማነው ከምቀኛ ጋር የሚተባበረው? ማነው የእርሱ ስኬታማነት ለእኔም ስኬታማነት ነው የሚለው? ማንም!!!
ፈረንጆቹ “The Meaning of Your Communication is the Response You Get” እንደሚሉት፡፡

No comments:

Post a Comment