Saturday, July 26, 2014

አርጋኖን : ዘ ሠሉስ

የሠራሁትን ኃጢአት ባስበው ልቡናዬ እጅግ ደነገጠብኝ፡፡
አእምሮ ሳለኝ አለል ዘለል እያልኩ በጽርዓት መኖሬን ባሰብሁት
ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ፡፡
የኃጢአቴን ብዛት በተቆጣጠርሁ ጊዜ ልቡናዬ እጅግ ደነገጠ አንድ
ሰዓት ስንኳን ኃጢአት ለመስራት አላቋረጥኩም፡፡
በሰውና መላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ፡፡
በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ፡፡
ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ፡፡ ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው
ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሣ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ
ብዬ፡፡
ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትቸይውን አንቺን አማላጅ
አገኘሁ፡፡ ዘወትርም ከኔ እንዳትርቂ ዐወቅሁ፡፡
እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም በሃይማኖት ያዝሁሽ
በመዳሰስ አይደለም በእደ ሕሊና ያዝሁሽ በእደ ሥጋ አይደለም፡፡
እደ ሕሊናየን ግን የሰው ኃይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና፡፡
የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም፡፡
ልትደገፊኝ ያዝሁሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደላይ ከፍ ከፍ
ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጅኝ ግን አይደለም፡፡
ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለዕድሜ ልክ ብቻ አይደለም፡፡ እናቴ ሆይ
ነፍሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ፡፡ ስለ
ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ
እንደ ወደቅሁም እቀር ዘንድ አትርሺኝ

No comments:

Post a Comment