Sunday, July 27, 2014

መሥዋዕቱን ማክበር

ወንድሞቼ ሆይ ! ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡

መልካም አድርጋችኋል፡፡

ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣

ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡

ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና

ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል ?

ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ

አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም?

ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን

ምን ይረባችኋል?

ምንስ ይጠቅማችኋል ?

ተወዳጆች ሆይ !

አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን

ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡

ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

ልብ በሉ ! ቤተክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤

ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡

ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡

እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

ክርስቶስን ማክበር ትወዳላችሁን ?

እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡

እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ

እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡

ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡

በቃሉ “ ይህ ሥጋዬ ነው ” ያለው ጌታ

በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ …

ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ይለናል

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

No comments:

Post a Comment