Thursday, July 24, 2014

ፍቅረኛ

ፍቅረኛውን ደውሎ እያናገራት ነው
ወንዱ:- ፍቅሬ
ሴቷ:- አቤት ማሬ
ወንዱ:- ለኔ ያለሽን ፍቅር በ1 ነገር ግለጪ
ብትባይ በምን ትገልጪዋለሽ
ሴቷ:- እንዴ ማሬ እኔ ላንተ ያለኝን ፍቅር
ሊገልፅ የሚችል አንዳችም ነገር ያለ
አይመስለኝም
ወንዱ:- በአንድ ነገር ግለጪ ብትባይስ
ሴቷ:- እሺ በቃ እኔ የሞባይል ቀፎ ነኝ አንተ
ደግሞ ሲም ካርድ ነህ ቀፎ ያለ ሲም ባዶ
እንደሆነ ሁሉ እኔም ያለ አንተ ባዶ ነኝ
ወንዱ:- በጣም ነው የምወድሽ ብሎ ስልኩ
ተዘጋ
ሴቷም ወደ ሰማይ ቀና ብላ ተመስገን
አምላኬ እንኩዋን ባለ ስንት ሲም ቀፎ
እንደሆንኩ አላወቀ አለች

No comments:

Post a Comment