Saturday, July 26, 2014

ቅዱስ ቂርቆስ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

ቅዱስ ቂርቆስ ፡ ሀገሩ ሮም አንጌቤን ነው


አባቱ ቆዝሚስ


እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ።

በዘመነ ሰማእታት በጨካኙ እና በአረመኔው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት አዋጅ ታውጆ ነበር፡፡ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትረሓዋ አብያተ ክርስትያናት ይትዐጸዋ›› ብሎ በ303 ዓም አዋጅ አወጀ ፡፡


በዚህ ግዜ ብዙ ክርስትያኖች ተሰደዱ ቅድስት እየሉጣም የ3 አመት ልጆን ይዛ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች ፡፡ ንጉስ እለ እስክንድሮስ አስጠርቶ ክርስቶስን ካጅ ለጣኦት ስገጅ አላት ፡ በእጅህ ሰርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች እምቢ ካልሽ... በሴፍ ትቀጫለሽ ብሎ አስፈራራት እርሳ ግን ምንም አልፈራችም እምነታችው ጠንካራ ነውና፡


በብረት ጋን ውሀ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሎ ብሎ አዘዘ ‹‹ድምጻ ለጽህርት ከመነጎድጎደ ክረምት ›› የውሀው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጎድ4- 15 ክንድ ያህል ይፈላ ነበር ፡ በፈላው ውሀ ሊጨምሮቸው ሲወስዶቸው የኢየሎጣ ልብ በፍርሀት ታወከ በዚህ ግዜ በቅዱስ ቂርቆስ ላይ መንፈስ ቅዱስ አድሮ የእናቱን ፍርት አስወገደ ፡፡


እናቴ ሆይ በርች ፣ጨክኝ አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ያዳነ አማለክ ያድነን የለምን እያለ እናቱን እያደፈፈረ ከእሳቱ ቀረበ እርሳም ጨክና በፍጹም ልቦ ተያይዘው ከፈላው ውሀ ገብተዋል፡፡


የመሰከሩለትን እና ያመኑትን የማይተው አምላክ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውሀ አቀዝቅዞ አዳናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment