Saturday, July 26, 2014

ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

ጽንሃ

ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው ።

ሦስት ሰንሰለቶች አሉት በሰንሰለቶቹ ላይ

ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል ።

ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል አለው ።

ይህም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን ፥ መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል ።

ፍህሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ምዑዘ ባሕርይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያጠይቃል ።

ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው ።

የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው ።

ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ።

የአብ ጸጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ፈጣን ተራዳዒነት ጥበቃቸው የፃድቃን ሰማዕታት የቅዱሳን ሐዋሪያት የአበው መነኮሳት ምልጃ ጸሎት ቃል ኪዳናቸው ረድኤት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን !!"

No comments:

Post a Comment