Thursday, July 24, 2014

የቢሮዬ ስልክ

ባል የስልክ ሊከፍል ቴሌ ይሄድና 890 ብር
እንደቆጠረ ይናገረዋል፡፡ ይሄኔ በብስጭት
እየተጣደፈ ወደቤቱ ይሄድና በሩን በርግዶ
ይገባል፡፡
ባል፡- እኔ የዚህ ቤት ነገር እየበቃኝ ነው፤
በብስጭትና በድህነት እኔን ለመግደል
ሳትነሱ አልቀራችሁም፡፡ አሁን ከቴሌ የቤቱ
ስልክ 900 ብር ቆጠረ ተብዬ ነው
የመጣሁት… እኔ እንደሆነ ወሩን ሙሉ
ይሄን ስልክ አልተጠቀምኩም፤ ስልክ
መደወል ስፈልግም በቢሮዬ ስልክ ነው
የምጠቀመው … አስቸኳይ ነገር
ቢያጋጥመኝ እንኳን እንደምንም ጉዳዩን
አሳድሬ ስራ ቦታ ነው የምደውለው… ማን
ነው ስልኬን እንደልቡ ሲጫወትበትት
የከረመው???
ሚስት፡- ኧረ እኔ ምንም ደውዬበት
አላውቅም፤ መቼ ለት እንኳን ለአዲስ
አመት ዘመድ ወዳጆቻችንን “እንኳን
አደረሳችሁ” ልል ፈልጌ ሁሉንም በመስሪያ
ቤቴ ስልክ አዳርሼ ነው የመጣሁት…
ይሄኔ ባልም ሚስትም ወደ ቤት ሰራተኛዋ
ሰርኬ ዞር አሉ
ሰርኬ ፡ ኧረገኝ!!! ጋሽዬና እትዬ ደግሞ…
ምነው እኔ ላይ አፈጠጣችሁብኝሳ?? …
እኔም በመስሪያቤቴ ስልክ ነው
የተጠቀምኩት… ምን ታካብዳላችሁ?

source;- keshit yamarigna keldoch
ሚስት - ሆዴ በፊት እጮኛክ እያለሁ ስጦታ
ትገዛልኝ ነበር
ባል - እና
ሚስት - አሁን ግን ያን ማድረግ ትተሀል
ለምንድነው
ባል - አሳ አጥማጅ አሳውን እስኪይዘው ነው
ምግብ ሚሰጠው

No comments:

Post a Comment