Saturday, July 26, 2014

መቁዋሚያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
መቁዋሚያ ምሳሌነቱ ፦ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሸከመውና የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ምሳሌ ነው ።
በሥርዓተ ማህሌት ጊዜ መዘምራኑ
መጀመሪያ መቁዋሚያቸውን ከላይ ወደ ታች ያደርጉታል ።
ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ መወለዱን ያመለክታል
ከዚያም ዓለምን ዞሮ ማስተማሩን ለማጠየቅ መቁዋሚያውን ከግራ ወደ ቀኝ ያሽከረክሩታል ።
መዘምራኑ መቁዋሚያቸውን ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ የሚያደርጉት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐና ቀያፋ ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ መመላለሱን መከራ መቀበሉን ለመሳሳብ ነው ።
መቁዋሚያውን ወደ መሬት የሚደስቁት የማይሞት ጌታ ወደ መቃብር ወረደ ሲሉ ነው ። ወደ መሬት የደሰቁትን መልሰው ወደ ላይ ማንሳታቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱን ለመመስከር ነው ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀድሞ በበለጠ ከፍ አድርገው በኃላ ረጋ ብለው የሚመልሱት ዕርገቱንና ዳግም ምፅዓቱን ለማዘከር ነው ። ሞቶ የተነሳው ተነስቶም ያረገው ዳግመኛ ይመጣል ሲሉ ነው ።
የአብ ጸጋ የወልድ ቸርነት የመንፈስ ቅዱስ አንድነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ፈጣን ተራዳዒነት ጥበቃቸው የፃድቃን ሰማዕታት የቅዱሳን ሐዋሪያት የአበው መነኮሳት ምልጃ ጸሎት ቃል ኪዳናቸው ረድኤት በረከታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን አሜን አሜን !!!

No comments:

Post a Comment