Thursday, August 29, 2013

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/

ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በዚህ ዓለም ሲመላለስ በሆሳዕና ማግሥት ጌታችን ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አድርጓል፡፡ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡/ማቴ.21÷12-17፤ ማር.11÷17፤ ሉቃ.19÷45-46፡፡ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ እንደተገለጸው ይህንም ምሳሌ አለ "ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡" ሉቃ 13፡6 በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ወደ ቤተ መቅደስ ግብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን እንዳስወጣ ሁሉ፤ ዛሬ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል። ማቴ 3፡8 ስለዚህ አምከ ቅዱሳን ከእኛ የሚፈልገውን የመንፈስ ፍሬ እናፍራ። ገላ 5፡22



የዛሬዋ ዕለት ጌታ የዕጸበለስን ዛፍ ፍሬ አይኑርብሽ ብሎ የረገመባት ቀን ነው በመባል ይታሰባል..ይህች በጌታ የተረገመችው ዕጸለስ ፀጋው የበዛላቸው ብዙ ሊቃውንት ተርጉመዋታል..አትሳደቡ ብሎ ህግን የሰራ አምላክ ተራጋሚ ሆኖ ሳይኖን ለማለት የፈለገው..በበለሷ በኩል ሊያስተምረን ያሰበው ነገር ይህነው..አይሁድ ሁሉን ትምህርቱን በሚገባ አስተምሮዋቸው ነበር..ትምህርቱ የቃል ብቻ ነው እንዳይሉ ደግሞ በተዐምራት የታገዘ ነብር..እግዚአብሄር እኔ ብርሃን ነኝ ብሎ ያስተምራቸውና እዛው ዓይን አብርቶ ያሳያቸዋል..ደግሞም እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ ብሎ ያስተምራቸውና እዝያው ደግሞ እንጀራ አበርክቶ ያበላቸው ነበር..እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ ብሎ ሞትን አሸንፏል..ይህንን የጌታ ምግባር የተመለከተው በ4ኛው መቶ ክ/ዘ የነበረው ሳዊሮስ የተባለው ሊቅ እንዲህ ይላል..እግዚአብሄር ትንሽ ነገር ተናግሮ ትልቅ ነገርን ያደርጋል..ሰዎች ግን ብዙ ትትለቅ ነገሮችን ይናገሩና ትንሿን ነገር እነኳን ማድረግ ያቅታቸዋል..ክርስቶስ ግን እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ማለቱ ትንሽ ነገር ነው ማንም ሊለው ይችላልና..ነገር ግን ዓይንነ አብርቶ ብርሃንን መፍጠር ለማንም አይቻልም..እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ ማለት ቀላል ነገር ነው..ወደ ተግባር ሲመነዘር ግን ሙት ማስነሳትን ይጠይቃል.ህይወት ማደልን ይጠይቃል..ስለእዝህ ነው ሊቁ እግዚአብሄር ማንም ሊናገረው የሚችለውን ትንሽ ነገር ተናግሮ ትልቁን ነገር ያደርጋል ማለቱ..ስለሆነም አይሁድን በቃልም በተግባርም ካስተማረ በኃላ..ከእንገዲህ በኃላ ለሐጥያታችሁ ምክንያት የላችሁም..ስለሆነም በሊቃውንቱ አተረረጓገም በለሷን ክርስቶስ ፍሬ አይሁንብሽ ብሎ የተናገራት እስራኤላዊያንን ነው ይላሉ..ምክንያቱም ክርስቶስ በለሷን ሲያያት ቅጠሏ በጣም ያምራል..ነገር ግን ቀርቦ ሲያያት ፍሬ የላትም ቅጠሉ በራሱ የፍሬ ዋዜማ እንጂ ግቡ አይደለም..እስራኤላውያኑም ቢሆኑ ከሩቅ ሲያያቸው ብሉይ ኪዳንን ያምናሉ..የነብያቱን የነሙሴን ታሪክ ያውቃሉ..ለህጉም ተዠና ተቆርቋሪ ይመስላሉ..ቀረብ ብለው ሲያይዋቸው ምነም አይነት የዕምነት ፍሬ የለባቸውም..ስለእዚህ ነው በበለሷ በኩል አስታኮ ጌታ በሚስጥር ቤተ እስራኤላውያንን የተናገረው በማለት ሊቃውንቱ እነ ቅዱስ ዮሐነስ አፈወረቅ ሚስጥሩን ግልጽ ያደረጉት..ጌታም በመከጠል ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ..ቤቱም የአምልኮ ቦታነቱ:የፀሎት ቦታነቱ:የወንጌል ቦታነቱ ቀርቶ ቅልጥ ያለ የገበያ አዳራሽ ሆኖ አገኝው..ጌታም ቤቴ የፀሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አድርጋችሁታል ብሎ የሚሸጡትን ሁሉ ገለባበጠባቸው..እየገረፈም ከመቅደሱ አስወጣቸው..የህን ማድረጉ አንድም የቅዱስ መንፈሱ ማደርያ የሆነውን የእኛ የአዳም ልጆችን..ሐጥያት በቅደስ ሰውነታች ቆሽሾ ቢያገኝን ነውራችንነ ሁሉ እንዳራቀልን:እንዳፀዳን የሚገልጽ ነው..ከእዚህም የተነሳ አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመባት ሰኞም ይባላል..በማስቀጠል የነገው ዕለት ማክሰኞ ነው

No comments:

Post a Comment